Psalms 13

በአምላኩ የታመነ ሰው አቤቱታ

ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር።

1 እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ለዘላለሙ ትረሳኛለህ?
ፊትህንስ ከእኔ የምትሰውረው እስከ መቼ ድረስ ነው?
2ከሐሳቤ ጋር የምሟገተው፣
ልቤም ቀኑን ሙሉ የሚያዝነው እስከ መቼ ነው?
ጠላቴስ በእኔ ላይ የሚያይለው እስከ መቼ ድረስ ነው?

3 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ተመልከት፤
ስማኝም፤
የሞት እንቅልፍ እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ፤
4በዚህም ጠላቴ፣ “አሸነፍሁት” እንዳይል፣
ባላጋራዎቼም በውድቀቴ ደስ እንዳይላቸው ርዳኝ።

5እኔ ግን በጸናች ፍቅርህ እታመናለሁ፤
ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።
6ቸርነቱ በዝቶልኛልና፣
ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።
Copyright information for AmhNASV